[Forwarded from Tsegaye Ararssa]
ለግፈኛ መንግሥት መገዛት፣ ኃጢአት ነው፣ ጥፋት ነው!
=================
ለግፈኛ ሥርዓት መገዛት፣ የአማኝ ምግባር አይደለም።
ፍትህን ለሚያጓድሉ፣ ምስኪኖችን ("አባት የለሹን፣ መፃተኛውን፣ እና መበለቲቱን") የሚበድሉ፣ እውነትን በውሸት የሚሸፍኑ (ሰላም ሳይኖር ሰላምን የሚሰብኩ፣ ድል ሳይኖር የድል 'ትንቢት' የሚተነብዩ፣ ተድላ ሳይኖር ስለ ድሎት የሚመሰክሩ)፣ ወዘተ መሪዎችን አለመቃወም ከኢፍትሃዊነት ጋር መተባበር ነው።
ፍትህን የሚያጓድሉ፣ ሕግን የሚተላለፉ፣ በጉቦ ተደልለው ብቻ የሚወስኑ፣ በሰይፍ ምስኪኑን የሚያጠቁትን መሪዎች ("አለቆች፣ ፈራጆች፣ ካህናት፣ እና ነብያትን") ሁሉ ያለ ፍርሃትና ያለመከልከል የሚኮንኑ ነብያት የፃፉትን መጽሐፍ ይዘህ፣ "ለገዢዎች ተገዙ፣ ለመሪዎች ጸልዩ" ተብሏል የሚል ዝንጥል ጥቅስ ያለ አውዱ ማነበነብ ጽድቅ አይደለም። ቢያንስ ቢያንስ፣ ሊታዘዙት የሚገባና ሊታዘዙት የማይገባ አስተዳደር ልዩነት እንዳላቸው አለመገንዘብ ስንፍና ነው።
"የማሕበራዊ ወንጌል" (social gospel) ሰባኪ ነብያት ለዘመናት የሚቃወሙትን ግፈኛ አገዛዝ አለመቃወም ኃጢአት ነው። ግፈኛ መንግሥትን መታዘዝ፣ ለእርሱም መገዛት፣ ከግፈኞች ጋር መተባበር ነው።
ሕፃናትንና እናቶችን በጭካኔ የሚገድል፣ ንጹሁን ያለ ፍርድ በመንገድ የሚደፋ፣ ነፍሰ-ጡር ሴትን እና ወንዶች ሕፃናትን ሳይቀር በወታደር የሚያስደፍር (የሚያነውር)፣ በህያዋን ቤት ላይ አቃጥሎ የሚገድል የእሳት ነበልባል የሚለቅ፣ ለአገርና ለሕዝብ ግልጋሎት የተጉ ዜጎችን ለእስርና ለእንግልት የሚዳርግ፣ ዘወትር በአደባባይ (በቤተ-መንግሥት፣ በቤተ-መቅደስ፣ በፓርላማ፣ በሚድያ፣ በሕዝብ ፊት፣ ወዘተ) እውነትን ለመቅበር ውሸትን ያለ ምንም ይሉኝታ የሚናገርን 'መሪ'፣ እያየህና እየኖርከው ያለውን እውነት ይዘህ ለመቃወም የምግባር ብርታት (moral courage) ከሌለህ፣ ያንተ በፈጣሪ ማመን አለማመን ሆኗል።
እንዲህ ያለውን መሪ አለመቃወም የምግባር ኮስማናነት ብቻ ሳይሆን፣ በራስም፣ በማህበረሰብም፣ በአገርም ላይ መርገምን የሚጋብዝ ጥፋት ነው።
ገና ለገና አብይ ያንተ 'አጥቢያ' ልጅ ስለሆነ ብቻ፣ 'እሱ ጻድቅ ነው' ብለህ አብረኸው የምትቆም ከሆነም፣ ምክንያት-አልባ ወገንተኛ (በእዛኛው ሰፈር ቋንቋ ሲገለጽ ደሞ፣ መንደረኛ ወይም ዘረኛ) መሆንህን እያጸናህ ነውና፣ ይሄም ይቅርታ አያሰጥም።
እውነተኛ የወንጌል አማኝ ከሆንክስ፣ ለማህበራዊ ፍትህ (ለምስኪኑ፣ ለመበለቲቱ፣ ለመፃተኛው፣ እና ለአባት-የለሹ) ትቆማለህ። ለእውነት ትቆቆማለህ። እውነትን ትናገራለህ፣ ይሄንንም ትመሰክራለህ። ይሄን ማድረግ አለመቻል መንፈሳዊ ስንፍና ነው። ከሕገ-ወጦች፣ ከጉልበተኞች፣ ከጨካኞች፣ እና ከአምባገነኖች ጋር መቆም ነው፣ ከእነዚህ ጋር መተባበር ነው።
At least, get your theology right before you demand obedience to an illegitimate government.
#For_apologists_of_power!
#ለአሸርጋጅ_ጴንጤዎች!
#Abiy_must_be_removed!
By: via Qerro Media Service - QMS
No comments:
Post a Comment