የሽግግር/ጊዜያዊ መንግሥት ማቋቋም፣ ግዴታ እንጂ ምርጫ አይደለም። (It is not an option; it is a responsibility.)
ዛሬ የኢትዮጵያ የፖለቲካ ኃይሎች ሁሉ ያላቸው አማራጭ፣ ወይ የሽግግር (ጊዜያዊ) መንግሥት ማቋቋምና አገርን ወደ ምርጫ፣ ፖለቲካውንም ወደ ሕገ-መንግሥታዊ ምልክቶች (sign posts) መመለስ፤ ወይም ቁጭ ብለው ሕዝብ በሕገ-ወጥ አምባገነናዊ አገዛዝ ሥር እንዲማቅቅ፣ አገርም ወደ ለየለት ሥርዓተ-አልበኝነት (ምናልባትም ወደ ለየለት የእርስ በርስ ጦርነት) እንድትወርድ መፍቀድ ነው።
ዛሬ ከመዳከም ወይም ከግድ-የለሽነት የተነሳ፣ ሁለተኛውን አማራጭ እንደ አማራጭ ቢወስዱ እንኳን፣ ሄዶ ሄዶ ይሄ የአብይ ቡድን እብደት፣ ወንጀል፣ እና ትርምስ ሲያበቃ፣ ሥራ የሚጀምሩት ይሄንኑ ግዴታ በመወጣት--ማለትም፣ የሽግግር (ጊዜያዊ) መንግሥት በማቋቋም--ነው።
ስለዚህ ይህንን የማይቀርና አማራጭ የሌለውን ታሪካዊ ግዴታ ለመወጣት በመድፈር፣ በአስቸኳይ ጊዜያዊ መንግሥትን መስርቶ አደጋውን መቀነስ ይገባል።
It is not an option; it's a responsibility.
#Abiy_Ahmed_has_expired!
By: via Qerro Media Service - QMS
No comments:
Post a Comment