ስለ ምርጫ ሕገ-መንግሥታዊነት እንደገና
=======
1. ምርጫ ማካሄድ፣ ሕገ-መንግሥታዊ ግዴታን በተገቢው መንገድ መወጣት ነው። ምርጫን በተቀመጠለት የጊዜ ሰሌዳ መሠረት ማካሄድ፣ የአንድን ሕዝብ የዴሞክራሲ መብት (ማለትም፣ ሕዝቦች መንግሥታቸውን የማቆም፣ የመቆጣጠርና፣ ካልፈለጉትም የመሻር ሥልጣንን) ማክበር ነው።
የሕዝቦች የዴሞክራሲ መብት (the right of people to democracy)፣ ሥልጣን በመሠረቱ የመንግሥት ሳይሆን የሕዝብ መሆኑን ታሳቢ ያደረገ ነው። ይህ እሳቤ፣ መንግሥት ሥልጣንን የሚጠቀመው ሕዝብን ወክሎ ብቻ መሆኑን አስምሮበት ይነሳል። በመሆኑም፣ አንድ ሰው፣ ወይም አንድ ቡድን፣ መንግሥት ለመሆንና እንደ መንግሥትም ሥልጣንን ለመጠቀም እንዲችል፣ በቅድሚያ፣ በግልጽ በህዝብ መወከል አለበት። ይሄ የሕዝብ ውክልና ደሞ የሚረጋገጠው በምርጫ ብቻ ነው።
ያለ ምርጫ፣ ሕዝብን ወክሎ ሥልጣን መያዝም፣ መጠቀምም፣ የሥልጣን ዘመንን ማስረዘምም አይቻልም። ሕጋዊ መሠረትም፣ ፖለቲካዊ ቅቡልነትም አይኖረውም።
በኢትዮጵያ ሕገመንግሥት አንቀጽ 8 የተደነገገውም፣ ይህንኑ መርህ በግልጽ የሚያጸና ነው። ሥልጣን (መሠረታዊው የሉዓላዊነት ሥልጣን) የብሔር ብሔረሰቦችና ሕዝቦች መሆኑን፣ ይሄ ሥልጣንም መገለጫው ሕገ-መንግሥቱ መሆኑን፣ ሕገ-መንግሥቱ ከሚደነግገው አግባብ ውጪ በሌላ መንገድ ሥልጣን መያዝ እንደማይቻል በግልጽ ይደነግጋል። ይሄ ከሕገ-መንግሥቱ መሠረታዊ መርሆዎች አንዱና የመጀመሪያው ነው። ሕገ-መንግሥቱ ፣ ደግሞ በዝርዝር ድንጋጌዎቹ፣ ኢትዮጵያ የውክልና ዴሞክራሲ ሥርዓት እንዳላት፣ ይሄንንም ለመተግበር፣ የሕዝብ ተወካዮች በየአምስት ዓመቱ በሕዝብ እንደሚመረጡ፣ እነዚህ በህዝብ የተመረጡ ተወካዮች (ማለትም የፓርላማ አባላት)፣ መንግስት (የሥራ አስፈጻሚውን አካል) እንደሚያቋቁሙ፣ የፓርላማው (እና በፓርላማው የተቋቋመው መንግሥትም) የሥልጣን ዘመን አምስት ዓመት ብቻ እንደሆነ በግልጽ ያስቀምጣል (አንቀጽ 50፣ 54፣ 56፣ እና 58)።
2. የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት (የፌደራሉም ሆነ የክልሎች) የሥልጣ ዘመን 5 ዓመት መሆኑ በግልጽ ተቀምጧል። ይሄ በክልሎቹ ሕገ-መንግሥታት ውስጥም በግልጽ የተቀመጠ ድንጋጌ ነው።
ከዚህም የተነሳ፣ ምርጫ፣ ይህ የሥልጣን ዘመን ከማለፉ (ወይም 5ቱ ዓመታት ከማለቃቸው)(አንድ ወር) በፊት ተካሂዶ መጠናቀቅ አለበት።
ምርጫ ባልተካሄደበት ሁኔታ፣ ሥልጣን ማስረዘም የሚቻልበት አንዳችም ክፍተት የለም።
ያለ ምርጫ ሥልጣንን ለማራዘም ሲባል ብቻ የሚደረግ የትርጉም ፍለጋ ተግባርም ትክክል አይደለም፤ ምንም ሕጋዊ መሠረት የለውም።
3. በኮረና ምክንያት የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ የታወጀ በመሆኑ ምርጫ ለማድረግ ይቻል ወይም አይቻል እንደሆነ ለማወቅ ሕገ-መንግሥታዊ ትርጉም መጠየቁም፣ ያስፈልጋል ተብሎ መበየኑም፣ ፍጹም ሕጋዊነትም ሆነ ሕገ-መንግሥታዊነት ያለው አካሄድ አይደለም። ሕጉ በግልጽ "ምርጫ በየአምስት ዓመቱ ይካሄዳል" ካለ፣ እና ይሄን ተላልፈን ሥልጣን ማራዘም አለብን ከተባለ፣ ብቸኛው መንገድ፣ ሕገ-መንግሥቱን ማሻሻል ነው እንጂ የሕገ-መንግሥት ትርጉም መጠየቅ አይደለም። ሕግ ግልጽ በሆነ ጊዜ የሚያስፈልገው መተርጎም ሳይሆን መተግበር ብቻ ነው።
4. ይሄም ሆኖ፣ ጉዳዩ ለሕገ-መንግሥት አጣሪ ጉባኤ ሲመራ፣ መጀመሪያ ሊወሰን የሚገባው ጭብጥ "ትርጉም ያስፈልጋል ወይስ አያስፈልግም?" የሚለው ሆኖ ሳለ፣ ይሄንን በማለፍ ወደ "ትርጉም" ሥራ ተገባ። ለመተርጎምም እንዲቻል፣ የህገ-መንግሥት ሕግ ባለሙያዎች፣ የሕገ-መንግሥቱ አርቃቂዎችን፣ ወዘተ የትርጉም ሃሳብ እንዲያቀርቡ ተጠየቀ። አጣሪ ጉባኤው፣ እራሱ በሕገመንግስት ትርጉም ጉዳይ የመጨረሻ የሕግ ባለሙያዎች አካል ተደርጎ የሚወስድ ቅድመ-ግምት (presumption) መኖሩን ባለመገንዘብ፣ ከሌላ አካል የትርጉም ሃሳብ መጠየቁ ስህተት ነበር። ይሄ ተግባሩ፣ በኢትዮጵያ የሕግ ሥርዓት ታሪክ ውስጥ አሳፋሪ ሆኖ ሲታወስ ይኖራል።
የሕገ-መንግስት ትርጉም የሚያስፈልገው አንቀጽ ኖሮ፣ ትርጉም ያስፈልጋል ቢባል እንኳን፣ ከጉዳዩ ጋር የፍሬ ነገር ተያያዥነት ስላለው መሰማት ያለበት የሙያ ምስክርነት፣ የጤና ባለሙያዎችና የምርጫ ባለሙያዎች ሙያዊ የምስክርነት ቃል ብቻ ነበር።
የጤና ሚኒስቴር እና የምርጫ ቦርድ ሹመኞች ቀርበው የሰጡት ምስክርነት፣ ሕገ-መንግሥታዊ ትርጉም የሚያስፈልገው አንቀጽ የነበረ ቢሆን ኖሮ፣ ትክክለኛ የሆነ፣ የፍሬ ነገር ጭብጥ ለማስረዳት የሚጠቅም፣ ምስክርነት ነበር። በእነሱ ምስክርነት መሠረት፣ ምርጫ ለማድረግ አይቻልም የሚል መደምደሚያ ላይ ከተደረሰም፣ ትክክለኛው ቀጣይ ውሳኔ መሆን የነበረበት፣ የሕገ-መንግሥት ማሻሻያ እንዲደረግ ሃሳብ ማቅረብ ነበር እንጂ፣ ያለ ምርጫ የሥልጣን ዘመንን ማራዘም አልነበረም።
አጣሪ ገባኤው፣ ያለ ሥልጣኑ ኢ-ሕገመንግሥታዊ በሆነ መንገድ የአብይን መንግሥት የሥልጣን ዘመን ለማራዘም ያቀረበው የውሳኔ ሃሳብ ለፌደሬሽን ምክር ቤት ሲቀርብ፣ የወቅቱ የፌደሬሽን ምክር ቤት አፈ-ጉባኤ፣ የውሳኔ ሃሳቡን፣ ሕገ-መንግሥታዊ ስላልሆነ አለመቀበላቸውን በይፋ ገልጸዋል። በዚህም፣ የሕገ-መንግሥት ትርጉም ሥራን በሚመለከት የመጨረሻ ሥልጣን ያለውና የሕገ-መንግሥቱ ባለአደራ የሆነው የፌደሬሽን ምክር ቤት፣ ውሳኔውን ውድቅ አደረገው።
ይሄንን የውሳኔ ሃሳብ፣ አብይ በጉልበትና በድርጅታዊ ሴራ በምክር ቤቱ ላይ ለመጫን ጥረት ሲያደርግም፣ አፈ-ጉባኤዋ፣ ለሕገ-መንግሥቱ፣ ለፌደሬሽኑና ለሕዝቦቹ፣ እንዲሁም ለህሊናቸው ተገዢነታቸውን በመግለጽ፣ ከስልጣናቸው እራሳቸውን አግልለዋል። ይሄም ውሳኔው ተቀባይነት እንዳጣ፣ ሕገ-መንግሥታዊና ተቋማዊ መሠረትም እንዳላገኘ ግልጽ ያደረገ ክስተት ነበር። ጥልቅ የሆነ የሕገ-መንግሥት ቀውስ ሁኔታ በገሃድ የተከሰተበት ወቅትም ይሄ ወቅት ነበር።
6. መንግሥታዊ ሕገ-ወጥነቱ ቀጥሎ፣ በይፋ ህገ-መንግሥታዊ ሥርዓቱን ከሥሩ መሸርሸሩ እየተስፋፋ፣ አፈ-ጉባኤዋ በተቃውሞ የለቀቁትን የፌደሬሽን ምክር ቤቱን በመጠቀም፣ የአብይ መንግሥት የፌደራሉን ብቻ ሳይሆን የክልሎችን ምርጫም ላልተወሰነ ጊዜ አስተላለፈ፤ ያለ ምርጫም የአብይን መንግሥት የሥልጣን ዘመን አራዘመ። ባልቀረበለት የክልሎች ሕገ-መንግሥታት ላይም "የትርጉም" ሥልጣን ያለው ይመስል በማይመለከተው ጉዳይ ገብቶ የክልሎቹን ምክር ቤቶች የሥልጣን ዘመን አራዘምኩ አለ።
ይሄን ተከትሎም፣ ለወትሮውም ቢሆን ምርጫ እንዳይካሄድ ሲወተውት የነበረው ምርጫ ቦርድ፣ በአብይ ትዕዛዝ፣ "ክልሎች ካለ እኔ ፈቃድ ምርጫ ማካሄድ አይችሉም፤ ምርጫ ማድረግ፣ ሕገመንግሥታዊ ሥርዓቱን አደጋ ውስጥ ስለሚከት፣ ክልሎች ምርጫ ለማድረግ ከተነሱም፣ የፌደራል ጣልቃ-ገብነት ትዕዛዝ በማውጣት አስቆማለሁ" ሲል ፎከረ።
7. በመሠረቱ፣
ሀ) ምርጫ ቦርድ በአንቀጽ 102 መሠረት፣ ምርጫ የማስፈጸም ሥልጣንና ኃላፊነት (ግዴታ) አለው እንጂ፣ ምርጫ የመከልከል ሥልጣን የለውም።
ለ)ምርጫ ቦርድ በአዋጅ፣ "ጠቅላላ ምርጫ" (ማለትም ለፌደራልና ለክልል ምክር ቤት አባልነት የሚካሄዱ ምርጫዎችን) የማስፈጸም ስልጣንና ግዴታ አለበት።
ሐ) ክልሎች፣ የትግራይ ክልል እንዳደረገው፣ ምርጫ እንዲያስፈጽምላቸው ሲጠይቁ "አልችልም" ብሎ ከኃላፊነት መሸሹ የሚያስጠይቅ ነው። በምንም ምክንያት ይሁን "አልችልም ወይም አልፈልግም" ካለ፣ ክልሎች ምርጫ እንዳያካሄዱ እንቅፋት መሆን አይገባውም፣ አይችልምም። ምርጫን ማደናቀፍ በወንጀል ያስጠይቃልና።
መ) ምርጫ ቦርድ፣ ምርጫ የማስፈጸም ሥልጣን አለ
By: via Qerro Media Service - QMS
Subscribe to:
Post Comments (Atom)
Featured post
Ethiopia’s controversial quest for the sea
https://ift.tt/4t29xJd Ethiopia is famously landlocked. That’s why the ambitious Ethiopian prime minister Abiy Ahmed has long harbored visi...
-
Has your daily walk become an endless trudge to nowhere? These podcasts, chosen by comedians, podcasters, Guardian writers and readers, are ...
-
The actor’s remarkable life fed into the character of Arlette in the Netflix hit, from growing up Jewish in occupied France, via Left Bank j...
-
They are benevolent vegetarian gods. They watch over, through shielded eyes, the very few animals that have a fringe. William Topaz McGonag...
No comments:
Post a Comment