Qerro Media Service - QMS's Post

የአንድ አይነት ኃይሎችን ሊንናደድባቸው ሳይሆን ሊናዝንላቸው ይገባል፡፡ ይህን የሚንለው ከነርሱ እይታ ነገሮችን ያየን እንደሆን ነው፡፡ በመጀመሪያ የአንድ አይነት ኃይሎችን በሁለት መክፈል አለብን፡፡ የመጀመሪያው ካለፈው ሥርዓት ያተረፈው ነገር ቢኖር የባህል፣ የቋንቋና የታርክ የበላይነት ብቻ ሲሆን እስከአሁን ድረስ ጫማ እንኳ የሌለው ብዙሃኑን የሰሜኑን ማህበረሰብ ይመለከታል፡፡ሁለተኛው በቅኝ በተያዘው አገር ሰፍሮ የሚገኘው የአንድነት ኃይል ነው፡፡

የአንድ አይነት ኃይሎችን የነበራቸውን የእምነት፣ የአስተዳደር እና የመሬት ይዞታ ከቀዳማዊ ኃይለስላሴ ሥርዓት ጋር አብሮ ተንኮታኮተ፡፡ ሲሶ ለቀዳሽ፤ ሲሶ ለአንጋሽ ላይመለስ ተንኖ ጠፋ፡፡ የሀይማኖት እኩልነት ለመጀመሪያ ግዜ ተረጋገጠ፡፡

ደርግ ሲመጣ፣ የአገር አቅኚ ልጆች የተሻለ ትምህርት እና የአማርኛን ቋንቋ ይችሉ ስለነበር ቢሮክራሲውን በመቆጣጠር የባህል ልዕልናቸው አስጠብቀው መቀጠል ቻሉ፡፡ ሌላውንም የነርሱን ባህል አዳማቂ እንድሆን አደረጉ፡፡ ደርግ ሲወድቅ የብሄር ፖለቲካው ከክልሎች ቢሮክራሲ ላይ ነቅሎ አወጣቸው፡፡ (በአንድ ቋንቋ መቸከል ትርፉ ከስራ መባረር ሆነ)፡፡

እነኚህ የአንድ አይነት ኃይሎች በመሰባሰብ የፌዴራሉን፣ የፌዴራል ከተሞችን ቢሮክራሲ በረቀቀ ሁኔታ ተቆጣጠሩት፡፡ (ምንም እንኳ ኢህአዴግ የብሄር ተዋጽኦ በማለት ትግሬዎችን፣ ኦሮሞዎችን እና ደቡቦችን በቢሮክራሲው ውስጥ ማስገባት ቢቻለውም፤ አሁንም የአንድ አይነት ኃይሎች ቁጥር ከሌሎቹ ድምር ይበልጣል)፡፡ ሌላው የአንድ አይነት ኃይሎች ስትራቴጂ የነበረው ዋና ዋና የሚባሉ ከተሞች ላይ በመስፈር የአገልግሎት ዘርፉን መቆጣጠር (service sector) ይገኝበታል፡፡ ለዝህም ነበር በቅንጅት ግዜ በሁሉም ትላልቅ ከተሞች (ማለት ይቻላል) ማሸነፍ የቻሉት፡፡ ይህም ራስ ምታት የሆነበት ኢህአዴግ የከተሞችን ዴሞግራፊ መቀየር የተጀመረው 97ቱ ምርጫ ማግስት ነበር፡፡ የአዲስ አበባውም ዕቅድ ተይዞለት እየተሰራበት እንደሆነ ሽመልስ አብዲሳ ነግሮናል፡፡

የሀጫሉን ሞት ተከትሎ በኦሮሚያ የተነሳው ረብሻ መንግስት እንደፈለገው ውጤት ሳያመጣለት ቀርቷል፡፡ የተፈለገው ኦርቶአማራው ላይ ግድያ፣ ዘረፋ፣ እና ንብረት ውድመት በማካሄድ “አክራሪ ሙስልሞች” ናቸው የፈጸሙት ወደሚል ድምዳሜ በመድረስ ኦሮሞን በሀይማኖት ለመከፋፈል እና ለመምታት የተኬደበት መንገድ ውሃ የሚቋጥር ሊሆን አልቻለም፡፡ በተቃራኒው ግን የአንድ አይነት ኃይሎችን በኦሮሚያ ውስጥ ንብረት እንዳያካብቱ፣ ያላቸውን ሽጠው እንድወጡ እያደረጋቸው መሆኑን በቲቭ ከሚጠየቁት ሰዎች መረዳት ይቻላል፡፡ ሌላው ከኦሮምያ እየለቀቀ ያለው ምሁራንም ቁጥር እያደገ መምጣቱ ማንም ሰው አያጣውም፡፡

የአንድ አይነት ኃይሉ አሁን የቀረው በፌዴራል ውስጥ ያለው ጠንካራ ቢሮክራሲ መጨበጡና እና አንድ ክልል ማስተዳደሩ ብቻ ነው፡፡ ሌሎች ቋንቋዎች፣ የፌዴራል ቋንቋ በሚሆኑበት ግዜ የቋንቋውን የበላይነት እየከሰመ ይመጣል፡፡ የታርክ የበላይነቱን ደግሞ ሌሎች ብሄሮች የተማሩና የነቁ በመሆናቸው የሚቀርብላቸውን “የድቃላ ነገስታት” ታርክ የሚሰሙበት ጆሮ የላቸውም፤ ይበልጥ የአንድ አይነት ኃይሉን ታርኩ ካላሳፈረው በስተቀር፡፡ ስለዝህ የአንድ አይነት ኃይሎች አብይን እንደሙሴ ተመልክተዉት ሲያበቁ እሱን “7ኛ ንጉስ” አድርገው በማንገስ፣ ብልጽግናን ሀገር አቀፍ በማድረግ የተወገደውን ክፍለ ሀገሮች መልሰው ለማዋቀር ቢያስቡ ምን ጥፋት አለባቸው? በዝህም መልሰው የባህል፣ የታርክ፣ የቋንቋ እና የሀይማኖት የበላይነትን በግዜ ሂደት መልሰን እንቀዳጃለን ብለው ያልማሉ! ለዝህም ነው ተረታቸውን የሙጥኝ ብለው የያዙት፡፡ Forward thinking or farfetched?

መፍትሄ የሚሆነው ተረት ተረታቸው ዬትም እንደማያደርስ አውቀው፤ ኢትዮጵያ የነርሱ ብቻ ሳይሆን የሁላችንም መሆኗን ተቀብለው፤ እኩልነትን ፈቅደው፤ የሌላውንም ባህል እና እምነት የኢትዮጵያ መሆኑን ካመኑ ተባብረን ኢትዮጵያን ማዳን እንችላለን፡፡ በዝህ ህልማቸው የሚቀጥሉ ከሆነ ከማንም በላይ ተጎጂዎች ይሆናሉ፡፡ ስለዝህ እባካችሁ ቀልብ ግዙ፤ ስሜታዊነት እንዳያጠቃሁ ማለት አለብን! ( Rajo Media )

By: via Qerro Media Service - QMS

No comments:

Post a Comment

Featured post

Ethiopia’s controversial quest for the sea

https://ift.tt/4t29xJd Ethiopia is famously landlocked. That’s why the ambitious Ethiopian prime minister Abiy Ahmed has long harbored visi...