Qerro Media Service - QMS's Post

ወንጀለኛ፣ የፖለቲካ መፍትሔ የለውም!
==================
አብይ፣ ብልጥግና፣ እና እንደ ኢዜማ ያሉ ማህበርተኞቻቸው በሙሉ ወንጀለኞች ናቸው። ሌላው ቢቀር፣ ከSeptember 2018 ጀምሮ ለፈጸሙት ወንጀል፣ እያንዳንዳቸው፣ በየደረጃቸው ፍርዳቸውን ያገኛሉ።

በጉልበት ሥልጣን ለመያዝና የጉልበት 'ፖለቲካን' "ፖለቲካ ነው፣ አገርን ማዳን ነው ፣ ወዘተ" ከሚሉ ባለ ጊዜ ነፍጠኞች ጋር የሚደረግ የፖለቲካ ሥራ (political engagement) የለም። ለነፍጠኛ ተገቢው ምላሽ ነፍጥ፣ ለሰፈር ጉልቤም ተገቢው መልስ፣ ጉልበት ብቻ ነው።

በአብይ የሚመለስ የፖለቲካ ጥያቄ የለንም። (አብይ፣ በግልጽ እየተናገረም፣ በተግባርም እየፈጸመ ያለው፣ ከጠላትነት የመነጨ የኃይል ተግባር ነው። እነ ኢዜማም፣ በእሱ ተከልለው--by proxy--የዘመናት ጠላትነታቸውን እየተገበሩት ነው--እስካሁን በሚፈልጉት መጠን ባይሆንም።)

ከዚህ በኋላ፣ የኦሮሞ ሕዝብም ሆነ መላው የኢትዮጵያ ጭቁን ሕዝቦች፣ ከአብይና ከማህበርተኞቹ የሚጠብቁት ፖለቲካዊ ምላሽ የለም።

አብይ፣ ለፖለቲካ ጥያቄዎች ያለው መልስ፣ ብረት ብቻ መሆኑን ደግሞ ደጋግሞ በተግባር አሳይቷል፤ ደግሞ ደጋግሞም ተናግሯል።

አብይ፣ በሕዝቦች ላይ በጠላትነት--በአንጻር--በመቆም፣ በወታደር፣ በ(ልዩ)ፖሊስ ኃይል፣ በሰላዮች፣ በሚሊሽያ፣ በመንደር ካድሬ፣ በ'ብሔራዊ' ምርጫ ቦርድ፣ በከተማ ወንጀለኛ ቡድኖች፣ በሚድያ ደቦ፣ በምንደኛ የማህበራዊ ድረ-ገጽ 'አክቲቪስቶች'፣ እና በቤተ እምነቶች (በተለይ በብልጥግና ወንጌል ሰባኪዎች)፣ በኩል፣ የተደራጀ የጠላት አሰላለፍ በመያዝ፣ በብሔር ብሔረሰቦች እና ሕዝቦች ላይ ያላሰለሰ ጦርነትን አውጆአል።

ይህ ቡድን እስኪወገድ ድረስ፣ ይሄ የወንጀለኛ ቡድን የሚመራው መንግሥትም የኦሮሞ (እና የመላው ጭቁን ሕዝቦች ሁሉ) ጠላት ስለሆነ፣ ከዚህ መንግሥት የሚመጣ ፖለቲካዊ መፍትሄም፣ ሁለንተናዊ የሕዝቦች እፎይታም አይኖርም።

ይሄ ወንጀለኛ መንግሥት፣ ፖለቲካዊ መፍትሄ ለመስጠት የሚያስችል ፖለቲካዊ ቁመና የለውም።

መፍትሔው፣ ለሁለንተናዊ አገራዊ እፎይታ፣ ለዘላቂ ሰላም፣ እና ለሕዝቦች መብት መከበር ሲባል፣ አብይንና ማህበርተኞቹን በአስቸኳይ ማስወገድ ብቻ ነው።

አዎን፣ አብይ መወገድ አለበት። የሕዝቦች ሉዓላዊነትን ማዕከል ያደረገ የአገር ደህነነት አደጋ ነውና። የሕዝብ የሥልጣን ባለቤትን የማይቀበል፣ የዲሞክራሲ እንቅፋት የሆነ፣ የብሔሮች ሉዓላዊነት ጸር፣ የሕዝቦች ሕገመንግሥታዊ (የግልና የወል) መብቶችን የሚጥስ፣ ፍጹም ሕግና ምግባር የማይገዛው ቡድን ነውና።

#Abiy_must_be_removed!
#Abiy_is_the_past.
By: via Qerro Media Service - QMS

No comments:

Post a Comment

Featured post

Ethiopia’s controversial quest for the sea

https://ift.tt/4t29xJd Ethiopia is famously landlocked. That’s why the ambitious Ethiopian prime minister Abiy Ahmed has long harbored visi...