Daniel dhaba, [25.08.20 18:43]
ሕዝባዊ አመጽ እና የአምባገነኖች አወዳደቅ።
የአምባገነናዊ ሥርዓትን ለሚፋለሙ ወጣት ቄሮዎች፣ቀሬዎች፣ኢጀቶዎች፣ የላጋዎች፣ ዘርማዎች ..........በሙሉ።
ፕሮፌሰር George B. N. Ayittey, ጋናዊዉ ኢኮኖሚስትና ደራሲ በአፍሪካ አምባገነኖች ላይ ከፍተኛ ጥናት ያደረገ ሰዉ ነዉ። «Defeating Dictators», Fighting Tyranny in Africa በሚለዉ መጽሓፉ፣ ስለአምባገነኖች አወዳደቅ በሰፊዉ ጽፏል።
ጆርጅ አይቴ ዲክታተሮች በአብዘኛዉ የሚወድቁት ራሳቸዉ በሚፈጥሩት የተፈጥሮ ሕግጋት መዛባት፣ የዉስጣዊ ተቃርኖዎችና አሻጥሮችን በመፍጠር መሆኑን ይገልጻል። እነዚህ አሻጥሮች ሕዝቦችን ከፋፍሎ ለመግዛት ሲሉ በሕዝቦች መካከል ያለዉን አብሮነት (harmony) ያዛባሉ። ለምሳሌ አሁን ኢትዮጵያ ዉስጥ እንደሚደረገዉ አማራን ከኦሮሞ፣ እስላሙን ከክርስቲያኑ፣ ወይም አንዱን ሐይማኖት ከሌላዉ ሐይማኖት ጋር እንድጋጭ ያደርጋሉ። በአሁኑ ጊዜ በምስራቅ ኢትዮጵያ ምንም ያላጠፉትን ሼኮችን መግደሉ የዚህ ዓይነት ተልእኮ ያለዉ ሳይጠናዊ ሥራ ነዉ።
አንዱን ብሔር ከሌላዉ ብሔር ወይም የአንድን ብሔረ ሰብ አባላትን እርስ በርስ በማጋጨት በሕዝቦች መካከል ያለዉን አብሮነት በመሸርሸር አገሪቷን ራሳቸዉ ያዳክሟታል። አምባገነኖች ለሥልጣን ብቻ ስያስቡ ሳያዉቁት ኢኮኖሚው collapse ያደርጋል። በዚያ ላይ ደግሞ አሁን ቄሮ የወሰደዉ ዓይነት የኢኮኖሚ ማዕቀብና መንገድ መዝጋት /roadblock/ የአምባገነኖችን ዉድቀት ስለሚያፋጥን መንገድ መዝጋቱ ተጠናክሮ መቀጠል አለበት። The demise of the dictatorial regimes starts sooner when its economy begins to flatter.
በጣም ጨካኝ እና አረመኔያዊ አምባገነኖች የሚወድቁት እንዴት ነዉ?
የዚህን ጥያቄ መልስ ለማግኘት ከሥር የተለጠፈዉን ስለአምባገነኖች የሚተርከዉን ቪዲዮ አዳምጡ። እኔም ትንሽ ቀንጨብ አድርጌ ከዚሁ ቪዲዮ የወሰድኩትን ከዚህ እንደሚከተለዉ አቀርባለሁ።
ሕዝቦች ጭቆና ሲበዛበቸዉ ጭቆናዉን ለመቋቋም በብዛት ሆነዉ በመደራጀት ሕዝባዊ ተቃዉሞ (civil disobedience) ያስነሳሉ። አምባገነኖችን ለማስወገድ ሠላማዊ ተቃዉሞ (peaceful resistance) ከፍተኛ ዉጤት አለዉ። ሕዝባዊ ተቃዉሞ ከፍተኛ የሕዝብ ብዛትና መደራጀትን ይጠይቃል። በመቶና በሺዎች የሚቆጠሩ ተቃዋሚዎች በአምባገነኖች ላይ ብዙም ጫና አይፈጥሩም። ሕዝቦች በሚሊዮኖች ሆነዉ በሕብረት ሲነሱ የአምባገነኖች ጉልባትና ሥልጣን መፈረካከስ ይጀምራል። ለዚህም ነዉ አምባገነኖች ላይ በተናጠልና በተበታተነ መልኩ ተቃዉሞ ማድረግ ዉጤት የማያመጣዉ። አንድ ጊዜ ሲዳማ፣ ሌላ ጊዜ ወላይታ፣ ሌላ ጊዜ ካምባታ ወይም ጉራጌ በመንግስት ላይ ቢያምጹ በአጭር ጊዜ ዉጤት ላያመጡ ይችላሉ። ለምሳሌ እንደ ኦሮሞ በብዙ ሚሊዮን ከሚቆጠር ሕዝብ ጋር ትግላቸዉን በጋራ ቢያደርጉ ደግሞ የአምባገነኖች ዕድሜ በአጭር ጊዜ ሊያበቃ ይችላል።
አሜሪካዊዉ የcivil Rights Activist ብዛትም ብቻዉን በቂ አይደለም ይላል። ከፍተኛ ዲሲፕሊን፣ በቂ ልምምድ/ሥልጠና፣ ጥሩ ስትራቴጂና ጥሩ ዕቅድ እንደሚያስፈልግ ይናገራል። እንደዚሁም የደቡብ አፍሪካዊ ጸረ አፓርታይድ መሪ Mkhuseli Jack, አንዱ የሰላማዊ ተቃዉሞ ዓላማ የአለምን አትኩሮ (attention) በተቻለ መጠን ለመሳብ መሆኑን ይናገራል። ቄሮዎችና ቀሬዎች በአሜሪካና በአዉሮፓ አንዳንድ የኢትዮጵያን ኤምባሲ አዘግተዉ የሚያደርጉት ትግል የዚህ ዓይነት ዓላማ ያለዉ ነዉ።
ከተቃዉሞ ዓይነቶች አንዱ በመንግስት ተቋማት ላይ ማዕቀብ መጣል ነዉ። ለምሳሌ ባንክ፣ እንሹራንስ፣ የንግድ ተቋማት በመሳሰሉት ላይ ማዕቀብ መጣልና ግብር አለመክፈል ናቸዉ። ለምሳሌ በአፓርታይድ ደቡብ አፍሪካ በነጭ ባለሀብቶች ላይ ማዕቀብ በመደረጉ ድርጅታቸዉ ወደ መክሰር በመቃረቡ በመጨረሻ የጥቁሮችን ተቃዉሞ ተቀላቅለዉ ለዉጡ ቶሎ እንዲመጣ አስተዋጻኦ አድርገዋል።
በሕዝባዊ ተቃዉሞ ዉስጥ የግዴታ ታዋቂ መሪ (charismatic leader) አያስፈልግም። ብዙዎቹ ሕዝባዊ ተቃዉሞዎች የጋንዲ እና የማርቲን ሉተር ክንግ ዓይነት መሪ ኖሮአቸዉ አይደለም። ለምሳሌ በቺሌና በሰርቢያ የዚህ ዓይነት ታዋቂ መሪ አልነበራቸዉም። በአገራችንም ጀዋር ከታሰረ በኋላ የቄሮዎች ንቅናቄ የሚቆም የመሰላቸዉ የመንግስት አመራሮች አልጠፉም። እንዲያዉም እንደ ጀዋር ዓይነት ታዋቂ አመራሮች ለእስራት ስለሚጋለጡ የሕዝባዊ አመጽ አመራሮች በስዉር የሚንቀሳቀሱ በርካታ አመራሮች መኖር አለባቸዉ። እንደዚያ ሲሆን መንግስት ሁሉንም መግደል ወይም ማሰር አይችልም።
አንዳንድ ጨካኝና አረመኔያዊ አምባገነኖች ፖሊስና መከላከያዉ በእጃቸዉ እስካለ ድረስ ቶሎ እጃቸዉን ላይሰጡ ይችላሉ። የቺሌዉ የፕሮ ዴሞክራሲ አክቲቪስት Christian Precht, መንግስት የኃይል እርምጃ መዉሰድ ከጀመረ፣ ተቃዋሚዎችም ባላቸዉ አቅም የኃይል እርምጃ ለመዉሰድ ይገደዳሉ ይላል። ለምሳሌ መንገድ መዝጋት ወይም መቁረጥ፣ ድልድይ ማፍረስ፣ ዉሃና መብራት እስከ መቁረጥ ድረስ ይገደዳሉ። በሰላማዊ መንገድ መታገል መንግስት ሰላማዊ ሰልፍ ማድረግ ከፈቀደና ለሰልፈኞቹም በፖሊስ ጥበቃ ካደረገ ብቻ ነዉ።
የሰርቢያዉ የተቀዋሚዎች መሪ Ivan Marcovic ብዙ ጊዜ አምባገነኖች የሚሳሳቱት የኃይል እርምጃ በጨመሩ ቁጥር ተቃዉሞዉን የሚያስቆሙ ይመስላቸዋል። ነገር ግን መንግስት የኃይል እርምጃ በጨመረ ቁጥር ተቃዉሞውም በዚያዉ መጠን በእጥፍ እየጨመረ ይሄዳል ብሏል። ከNewton's third law ጋር ያመሳስለል።
ሕዝባዊ ተቃዉሞ አምባገነኖችን ለማሳመን ሳይሆን ለማስገደድ ነዉ። ለዚህም ሲባል የኢኮኖሚ ማዕቀብ መድረግ ወይም ማህበራዊ ኑሮን በማቃወስ ለምሳሌ መንገድ በመዝጋት፣ መንገድ በመቁረጥ፣ መብራትና ዉሃ በመቁረጥ ሁኔታዎችን ከመንግስት ቁጥጥር ዉጪ በማድረግ ነዉ። መንግስት ወደ ኃይል እርምጃ ከገባ ተሸናፊዉ ራሱ መንግስት ነዉ።
ሕዝቦች በመንግስታቸዉ ላይ ያለዉ እምነት ሲመናመን አብዘኛዉ ሕዝብ የለዉጡ ደጋፊ ለመሆን ይገደዳል። ሌላዉ የሰርቢያ የተቃዋሚዎች መሪ Slobodan Djinovic ተቃዋሚዎች ለሚወስዱት እርምጃ መንግስት ምን ዓይነት አጸፋ እንደሚወስድ መገመትና አማራጮችን ማዘጋጀት አስፈላጊ መሆኑን ይናገራል። በመሆኑም 3 እርምጃ ቀድሞ በማሰብ የዛሬ 6 ወር ምን ዓይነት ሁኔታ እንደሚፈጠር መገመት መቻል አለባቸዉ ይላል። ለምሳሌ ዛሬ ላይ የሚደረገዉ የኢኮኖሚ ማዕቀብ ዉጤቱ የሚታየዉ ከ6 ወር በኋላ ሊሆን ይችላል። ስለዚህ አሁኑኑ ዉጤት ጠብቀዉ ቶሎ ተስፋ መቁረጥ አያስፈልግም ለማለት ነዉ።
እንደዚሁም ሌላዉ የቺሌዉ የፕሮ ዴሞክራሲ አክቲቪስት Sergio Bitar, መንግስት ለሚወስደዉ የኃይል እርምጃ ተቃዋሚዎችም በተቻላቸዉ መጠን ተመሳሳይ የኃይል እርምጃ ለመዉሰድ እንደሚገደዱ ይናገራል። ይህም ወደ ትጥቅ ትግል መግባት ሲሆን ይህ ስትራቴጂ ከፍተኛ ሥልጠና፣ ገንዘብና ትጥቅን ስለሚጠይቅ የበለጠ የሚያዋጣዉ ከፍተኛ ሰላማዊ እንቅስቃሴ (mass movement)ማድረግ መሆኑን ይገልጻል።
By: via Qerro Media Service - QMS
Subscribe to:
Post Comments (Atom)
Featured post
Ethiopia’s controversial quest for the sea
https://ift.tt/4t29xJd Ethiopia is famously landlocked. That’s why the ambitious Ethiopian prime minister Abiy Ahmed has long harbored visi...
-
Has your daily walk become an endless trudge to nowhere? These podcasts, chosen by comedians, podcasters, Guardian writers and readers, are ...
-
They are benevolent vegetarian gods. They watch over, through shielded eyes, the very few animals that have a fringe. William Topaz McGonag...
-
The actor’s remarkable life fed into the character of Arlette in the Netflix hit, from growing up Jewish in occupied France, via Left Bank j...
No comments:
Post a Comment