የኢዜማ መግለጫ አላማ
( By Segni Gudina )
1~>ፊንፊኔ ዙሪያ ከመሬታቸው ለዘመናት በግፍ ሲፈናቀሉ የነበሩትን የኦሮሞ ገበሬዎች ጥያቄ አቅጣጫ ማሳት፣ከመብታቸው በላይ እንደተጠቀሙና መሬት እንደወረሩ ማስወራት እና ገበሬውም በዚህ ተሸማቆ መብቱን እንዳይጠይቅ ማድረግ
2~>ከፊንፊኔ ጋር በተያያዘ የኦሮሞ ህዝብ ሲጠይቅ የነበረውን የባለቤትነት ጥያቄ ሌሎች ብሔር ብሔረሰብ የኦሮሞን ህዝብ ጥያቄ በጥርጣሬ እንዲመለከት ማድረግ፣ በዚህም "ኦሮሞ ሊወራቹ ነው!" ወይንም "ኦሮሞ ወራሪ ነው"ብሎ ሌሎች የኦሮሞን ህዝብ በፍራቻና በጥርጣሬ እንዲያይ፣ በዚህም የኦሮሞ ህዝብ እንዲሸማቀቅ ማድረግ
3~>እንደሚታወቀው ፊንፊኔ የኦሮሞ ህዝብ የትግል ማዕከል እና የኦሮሞ ህዝብ ከጫፍ እስከ ጫፍ በአንድነት የሚታገልበት ጉዳይ መሆኑ ይታወቃል፣ ይህንንም የትግል ማዕከል የሆነውን የፊንፊኔ ባለቤትነት ጥያቄ ማጠልሸት እና ማጥፋት፣
4~>የሚገርመው ለዘመናት የኦሮሞ ህዝብ ከገዛ ቄዬው ሲፈናቀል እና ባይተዋር ሆኖ ሲኖር ነበር፣ ይሄንንም ጭቆና ለማስቆም ላለፊት 4 አመታት ውድ ህይወቱን ሰጥቶ ታግሎ በተገኘው ለውጥ፣ ለዘመናት የታገለለት የባለቤትነት ጥያቄው ይመለሳል ብሎ እየጠበቀ ባለበት ሰአት የገዛ ልጆቹ በስሙ ስልጣን ይዘው፣በስሙ ምለው፣የዘመናት እንባህን እንጠርጋለን እያሉ በስሙ ነገዱ፣በስሙ ዘረፉ፣ በስሙ አዘረፉ፣ በስሙ ሁሉን ሌብነት ሰሩ፣
ይባስ ብሎ ለዘመናት መሬቱን በወረራ ሲቀራመት የነበረ የነፍጠኛው ስርአት ናፋቂ ሀይል "ኦሮሞ የኦሮሞን መሬት ወረረ" አይነት ጥናት ይዞ እንዲመጣ ከእነሱ ጋር ሆነው ከእነ ህይወቱ ሊቀብሩት አሴሩ!!
ዛሬም ነገም
፨የኦሮሞ ህዝብ የፊንፊኔን ባለቤትነት እስኪያረጋግጥ ድረስ ጥያቄውን አያቆምም፣
፨ለዘመናት ከገዛ ቄያቸው ዛሬም ድረስ የተፈናቀሉት የኤካ፣የቱለማ፣የአብቹ፣የገላን፣የግንቢቹ፣የጉለሌ የመሳሰሉት
የኦሮሞ ገበሬዎች አስፈላጊውን ካሳ ሁሉ ሊያገኙ ይገባል፣
፨የኦሮሞ ህዝብ ኢትዮጵያ ውስጥ ካለው አስተዋፅኦ እና ህዝብ ብዛት የሚመጣጠን የኢኮኖሚ ይሁን የፖለቲካ ስልጣን ለማግኘት በሌብነትም፣ይሁን በድብቅ የሚሰራበት አንዳች ምክኒያት የለውም!!!
ኦሮሞ የሚገባውን አላገኘም ፣ ከሚገባው በላይም አይፈልግም!!
ሌባ ብሔር የለውም!!!!
By: via Qerro Media Service - QMS
Subscribe to:
Post Comments (Atom)
Featured post
Ethiopia’s controversial quest for the sea
https://ift.tt/4t29xJd Ethiopia is famously landlocked. That’s why the ambitious Ethiopian prime minister Abiy Ahmed has long harbored visi...
-
Has your daily walk become an endless trudge to nowhere? These podcasts, chosen by comedians, podcasters, Guardian writers and readers, are ...
-
They are benevolent vegetarian gods. They watch over, through shielded eyes, the very few animals that have a fringe. William Topaz McGonag...
-
The actor’s remarkable life fed into the character of Arlette in the Netflix hit, from growing up Jewish in occupied France, via Left Bank j...
No comments:
Post a Comment