Qerro Media Service - QMS's Post

ጀዋር ሙሃመድ ዛሬ ፍርድ ቤት ከተናገረዉ

“ ልጃችን ሃጫሉን ገደሉት: መሪዎቹን አሰሩ : ሴቶቻችንን እየደፈሩ እና እየገደሉ ሰላም አይመጣም ሀገር እያፈረሳችሁ ያላችሁት እናንተው ናችሁ "
_
እኛ እድሜ ልካችንን የታገልነዉ ለፍትህ (እዉነት) ሆኖ የትግላችንን ዉጤት የህግ ባለሞያዎች የነገ ተስፈ ሲሆኑ እያየን ነዉ። ይህ ነገር ግን ወደታች ወርዶ አስከ ዞን እና ወረዳ መዉረድ አለበት። የመንግስት ተፅእኖ ያለባችሁ አቃቤ ህጎች አንዳላችሁ እንረዳለን። እናንተ ግን ለሙያችሁ እና ለፍትህ ታማኝ ሁኑ። ከፖለቲካ ተፅእኖ ገላልተኛ ሆናችሁ ስሩ። ለኛ ጥበቃ እያረጋችሁ ያላችሁ ፖሊሶች ክብር ይጋባችኋል ለምታረጉልን ጥበቃ እጅግ አርገን እናመሰግናለን። ይሄ ጥበቃ ግን እንደኛ እዉቅና ላላቸው ሰዎች ብቻ ሰይሆን ለሁሉም መሆን አለበት።ኦሮሚያ ላሉ እስረኞች ለሁሉም ታሳሪዎች መደረግ አለበት፤ ክብር እና ጥበቃም ስጧቸዉ። አትግደሏቸዉ አትደብድቧቸዉ።

ሌላው እኛ የፖሎቲካ እስረኞች ነን። እኛ የታሰርነዉ የመንግስት ሥልጣን ላይ ካሉት ጋር ካለን የፖለቲካ ልዩነት ነዉ። ሰዎችን በማሰር በመግደል እና ከሀገር እንዲሰደዱ በማድረግ ሰላም ሆና የቀጠለች ሀገር የለችም። ብዙ ሀገሮች በዚህ ሁኔታ ፈርሰዋል። እኛም የታሰርነዉ የ ኦሮሞን መብት አንሸጥም ስላልን ብቻ ነዉ። ኦሮሞን በማሰር የመጣ ለውጥ የለም። በብዙ ሺዎች የሚቆጠሩ ሰዎች የሚሰደዱት እዚህ ባለ እስር እና ግድያ ነዉ። ልጃችን ሃጫሉን ገደሉት መሪዎቹን አሰሩ ሴቶቻችንን እየደፈሩ እና እየገደሉ ሰላም አይመጣም ሀገር እያፈረሳችሁ ያላችሁት እናንተው ናችሁ።

መንግስት ይመጣል ያልፋል። ሀገር እንዲቀጥል ከተፈለገ ፍትህ ይስፈን እዉነት ይከበር። ፍትህ እዉነት ከ መንግስት ባለስልጣናት ሥልጣን በላይ ነዉ።
_
ትርጉም በ Shemsedin Abdukerim

Oromo Political Prisoners Defence Team
By: via Qerro Media Service - QMS

No comments:

Post a Comment

Featured post

Ethiopia’s controversial quest for the sea

https://ift.tt/4t29xJd Ethiopia is famously landlocked. That’s why the ambitious Ethiopian prime minister Abiy Ahmed has long harbored visi...