Qerro Media Service - QMS's Post

የማይመቹ እውነቶችንም ጭምር ለመስማት የምንችልበት ምግባር (ethics of listening to inconvenient truths) ለማሳደግ፣ የግዴታ ውል ከራሳቸው ጋር ሊገቡ ይገባል።

መ) የዕለት ተዕለት መንግሥታዊ ሥራን ማስተባበርን በተመለከተ፦ ጊዜያዊው መንግሥት፣ ለዘወትራዊ (routine ለሆኑ) የመንግሥት ሥራዎች (ማለትም የመንግሥታዊና ማህበራዊ ግልጋሎቶችን ፍሰት ለማስቀጠል፣ እንዲሁም ሕግና ሥርዓት ለማስፈን በሚወስዳቸው እርምጃዎቹ) ሁሉ ዋና መመሪያው፣ የአገሪቱ ሕገ-መንግሥትና ተፈጻሚነት ያላቸው መደበኛ ሕጎችና አስተዳደራዊ መመሪያዎች ሊሆኑ ይገባል። ጊዜያዊ መንግሥት፣ ዘላቂ ሕግጋትን የማጽናት እንጂ የመሻር መብትም ሥልጣንም የለውምና። የኋላ ኋላ ተጠያቂነቱም በሕገ-መንግሥቱና በህጎቹ መሠረት ይሆናልና።

ይሄንን ሁሉ ለማድረግ ደግሞ የትሁት ፖለቲካን መንገድ መከተል (ማለትም ማንም ከማንም የተሻለ መሲሓዊነት [Messianic] እና የማዳን ችሎታ እንደሌለው ማወቅ) የተገባ ነው። Memento Mori!

(በቀጣይ ጽሁፍ፣ ክልሎቹ ውስጥ ሊቋቋሙ ስለሚገባቸው የጊዜያዊ መንግሥታት ሁኔታ፣ እንደዚሁ፣ ጠቋሚ ነጥቦችን ለማንሳት እሞክራለሁ።)

(ይቀጥላል።)
By: via Qerro Media Service - QMS

No comments:

Post a Comment

Featured post

Ethiopia’s controversial quest for the sea

https://ift.tt/4t29xJd Ethiopia is famously landlocked. That’s why the ambitious Ethiopian prime minister Abiy Ahmed has long harbored visi...