Qerro Media Service - QMS's Post

ፕሬዚደንት ትራምፕ ግብፆች ህዳሴ ግድብን በቦምብ ሊመቱት እንደሚችሉ የሚጠቁም አስደንጋጭ ንግግር አድርጓል። ሱዳን ከ state sponsor of terrorism ጥቁር ዶሴ ስሟ እንዲፋቅ በግድቡ ድርድር ከግብፅ ጋር እንድትወግን በአሜሪካ ከፍተኛ ጫና ሲደረግባት ቆይቷል። July 21, 2020 በደቡብ አፍሪካው ፕሬዚደንት ሲሪል ራማፎዛ ሰብሳቢነት በተደረገ ውይይት የሶስትዮሽ ድርድሩ እንዲቀጥል ተወስኖ ነበር። በዚህም መሰረት ከ August 18 እስከ 28 የውሃ ሚኒስትሮችና ቴክኒካል ባለሞያዎች የበይነ መረብ ድርድር አድርገው ነበር።

FI የተመለከተው ከሳምንት በፊት circulate የተደረገ የውስጥ ሰነድ እንደሚጠቁመው ኢትዮጵያ ድርድሩን ከ September 14 ጀምሮ ካቆመበት ለመቀጠል ጥያቄ ብታቀርብም ሱዳን ከዚህ በፊት ያደረግነው ድርድር በቂ ነው በሚል ለመቀጠል ፈቃደኛ ሳትሆን መቅረቷን ይገልጻል። የመጨረሻው ድርድር (August 28) ከተደረገ ሁለት ወር አካባቢ ቢሆነውም ሱዳን እስካሁን ድርድሩን ለመቀጠል ፍላጎት አላሳየችም። ድርድሩ በእንጥልጥል እንደቀረ ነው። የዛሬው የትራምፕ ንግግር የሱዳን ልብ የሸፈተበትን ምክንያት ያሳያል። ሱዳን ግድቡ ትልቅ ጥቅም እንዳለው ብትረዳም የበለጠ value የምታደርገው ከሽብር ደጋፊ ሊስት ውስጥ መሰረዝን ነው። ዛሬ ከሊስቱ ውስጥ መሰረዟ ይፋ መደረጉ በግድቡ ላይ ከግብፅ ጎን ለመቆም መስማማቷን ጠቋሚ ነው። እንግዲህ ሱዳን ለግብፅ ከወገነች ድርድሩ ከእንግዲህ ብዙም ተስፋ አይኖረውም ማለት ነው።
-----
ትራምፕ ኢትዮጵያ እኔ ያዘጋጀሁላትን ዲል ሰብራለች (አልቀበልም ብላለች) ያንን ማድረግ አልነበረባትም ብሏል።

አሁን ቢያንስ ሶስት ሴናሪዮዎች (ቢሆኖች) አሉ

1. ትራምፕ ከአስር ቀን በኋላ በሚደረገው ምርጫ ተሸንፎ ባይደንና ሃሪስ ከተረከቡ ምናልባት ጫናው ሊቀንስ ይችላል። ይህም ቢሆን ትራምፕ እስከ ጃንዋሪ በስልጣን ላይ ስለሚቆይ አደጋው ለተወሰነ ጊዜ ይቀጥላል። ባይደን ስልጣን የሚይዝ ከሆነ ለውጭ ጉዳይ ሚኒስትርነት ከተገመቱት ሰዎች መሃል የቀድሞዋ የብሄራዊ ደህንነት አማካሪዋ #ሱሳን_ራይስ አንዷ ናት። ውጪ ጉዳይ ባትሆን እንኳን ሌላ ሁነኛ ቦታ መያዟ አይቀርም። ከወዲሁ ግንኙነት የሚፈጠርበትን መንገድ ማሰብ ጠቃሚ ነው። የመለስ ወዳጅ እንደመሆኗ ስለ ግድቡ በጎ እይታ እንደሚኖራት ይገመታል።

2. ትራምፕ ተጨማሪ አራት አመታት ካሸነፈ ግብፅ እንኳን ባትመታው አሜሪካ ተንቃለች በሚል ግድቡን በማናለብኝነት ሊመታው ይችላል የሚል ግምት መያዝ አለበት። አሜሪካን የሚጠይቅ የለም። ብዙ ሀገራትን አመድ አድርገዋል። ትራምፕ የሚቀጥል ከሆነ የአሜሪካን ውል እንደወረደ ካልፈረማችሁ ይላል ወይም ኢትዮጵያ ድርድሩ ላይ significant concession ለማድረግ ትገደዳለች። ግድቡ ከሚመታ ሙሌቱ ላይ ተጨማሪ አመታት መፍቀድ ይሻላል በሚል ብቻ ሳይሆን ለተጨመሪ አራት አመታት ያለ አሜሪካ የገንዘብ ድጋፍ መቀጠል ፈታኝ ስለሚሆን። የኢትዮጵያ ምጣኔ እድገት በዚህ አመት 1.9 በመቶ በሚቀጥለው ዜሮ ነው ማለቱ ከግምት ውስጥ ሲገባ የገንዘብ እቀባው ሰኔና ሰኞ ይሆናል። የኤክስፖርት ገቢ ያሽቆለቁላል፤ ሀብታም ሀገራት በኮቪድ አቅማቸው ስለተንኮታኮተ የአብይን ፓርክ ለመጎብኘት የሚመጣ ቱሪስት አይኖርም። በዚህ ላይ ተጨማሪ አራት አመታት የድጋፍ እቀባ ሲታከልበት ለመድሃኒት ማስገቢያ እንኳን የሚተርፍ የውጭ ምንዛሪ አይኖርም።

3. ምርጫውን ትራምፕም አሸነፈ ባይደን #ግብፅ ጥቃት የመሰንዘር እቅድ እንዳላት ትራምፕ እውነቱንም ይሁን ለማስፈራራት ነግሮናል። ይህ የወተደራዊ ጥቃት ስጋት መጠንን (military attack threat level) አንድ ደረጃ ከፍ የሚያደርግ ነው። ይህ ዜና ከተሰማበት ሰአት ጀምሮ ግድቡ በንቃት መጠበቅ አለበት። ሌላም ለጊዜው ያላሰብኩት ሊኖር ይችላል

-----
ያም ሆነ ይህ ወቀሳውን ለሌላ ጊዜ ብንመለስበትም እዚህ ቅርቃር ውስጥ የከተተን ሌላ ማንም ሳይሆን አብይ አህመድ ነው። ልክ የዛሬ አመት October 23, 2019 ነበር አብይ ለአፍሪካ-ራሺያ ሰሚት ወደ ሶቺ (Sochi) ባቀናበት ወቅት ከፕሬዚደንት #አልሲሲ ጋር ባደረገው የሁለትዮሽ ውይይት የአሜሪካን አደራዳሪነት የተቀበለው። የአሜሪካና የግብፅን ወዳጅነት የተረዱ በርካታ ሰዎች ተው ቢሉት አልሰማ ብሎ ውጤቱ ይሄ ሆነ። ዶ/ር ስለሺና አቶ ገዱ ይህ ታሪካዊ ስህተት እንዴት ሊወሰን እንደቻለ ለስማቸው ሲሉ ለህዝብ ማሳወቅ ይኖርባቸዋል። በዚህ ሁለት አመት ተኩል ውስጥ የዜጎችን ደህንነት በማረጋገጥም ሆነ በዲፕሎማሲው አብይ ከሽፋል ማለት huge understatement ይሆናል። ከኢሳያስ አፈወርቂ ጋር የሚደረግ ጉብኝትና ግብዣ እንደስኬት ካልተቆጠረ ማለት ነው።

~from The Finfinnee Intercept.
By: via Qerro Media Service - QMS

No comments:

Post a Comment

Featured post

Ethiopia’s controversial quest for the sea

https://ift.tt/4t29xJd Ethiopia is famously landlocked. That’s why the ambitious Ethiopian prime minister Abiy Ahmed has long harbored visi...