ስለ ሰሜኑ ጦርነት(ከሰፊው ደቡብ ተሳትፎ አንፃር)
(By Yared Estifanos)
****************
የኦሮሚያን ጨምሮ የሰፊው ደብቡ ብሄሬ እና ብሄሬሰብ ልጆች ስለዚህ ጦርነት ጠንቅቀን ልናውቅ ይገባል።
"ለማን ጥቅም እና ለምን አላማ ነው የሚካሄደው?" የሚለውን በደንብ ማጤን ያስፈልጋል። በሚዲያ ጋጋታ እና በካድሬ ወከባ እናዳንታለል።
የዚህ ጦርነት ጠንሳሽ እና አስፈፃሚዎች ሶስት ሃይሎች ናቸው፦
1#ኢሳያስ አፍወርቂ
ዓላማው፦
ህወሃትን መበቀልና ኢትዮጵያ ላይ አሻንጉሊት መሪ(አብይን) አደላድሎ በአከባቢው ፖለቲካ የበላይ ሆኖ መውጣት ነው።
በዚህም ሂደት ሰፊዋን ሃገር ኢትዮጵያ በማዳከም የራሱንና የሃገሩን ጥቅም(በኢትዮጵያ ዋጋ) ማረጋገጥ ይፈልጋል።
2#ተስፋፊ ርስት አስመላሾች
ዓላማቸው፦
ህገ-መንግስቱን በመቀዳደድ የህብረ-ብሄራዊ ፌደራል ስርዕቱን ማፍረስ ነው።
እኝህ ወገኖች ኢትዮዽያን በጠቅላላ አባቶቻችን ያቀኗት ርስታችን ናት ብለው ነው የሚያምኑት። ሌላውን እንደ ሃገር ባለቤት አያዩም። ደስ ሲላቸው ሰፊውን የኦሮሞ ህዝብ "ከማዳጋስካር የመጣ ነዉ" ይላሉ። ሶማሌውን፣ ጋምቤላውን ፣ ጉምዙን ወዘተ መጤ ይላሉ።
ከሃይማኖት አንፃርም አንድን ሃይማኖት የሃገር ባለቤት ሌላውን ተዳባይ አድርገው ነው የሚያዩት። ለምሳሌ ለዘመናት ሃገሪቱን የክርስቲያን ደሴት ናት በማለት ሙስሊሙን እና የሌሎች ሃይማኖት ተከታዮች ከሃገር ባለቤትነት እንዲጎድሉ ሲደረግ ተኑሯል። የዚያ አይነት ኢዲሞክሪያሳዊ አመለካከት ዛሬም ድረስ ሙሉ ለሙሉ አልተቀየረም ማለት ይቻላል። እንደነ ኢሬቻና ጨምበላላ የመሳሰሉ በዓላት በመጡ ቁጥር በሰፊው የሚታዩ ዘመቻዎችም የአካታች ስርዕት እና ባህል አለመኖር ችግር እንዳለ የሚያሳይ ነው።
ባጭሩ ይህ ርስት አስመላሹ ቡድን በእኩልነት ላይ የተመሰረተ የፌደራል ስርዕት ይኖር ዘንድ አይሻም። ትግሉም ለእኩልነት ሳይሆን ለበላይነት ነው።
ህዝቦች እራሳቸውን እና ቀያቸውን እንዲያስተዳድሩ አይፈልጉም። ቋንቋቸውም በየአከባቢዎቻቸውም ሆነ በፌደራል ደረጃ የስራ ቋንቋ እንዲሆን አይሹም። ይልቁኑ የፖለቲካ ችግሮቻችንን ሃጥያት ሁሉ በህብረ-ብሄራዊ ፈደራል ስርዕቱ ላይ በመደፍደፍ የክልል አደረጃጀትን ማፍረስ ይፈልጋሉ።
(ኔሽኖች የፖለቲካ ማህበረሰቦች ሳይሆኑ ትንንሽ የባህልና ቋንቋ ቡድኖች እንዲሆኑ ይፈለጋል። ይህ በቀጥታ ሃገሪቱን የአንድ ቋንቋና ባህል (በመዋቅር ደረጃ) ያደርጋታል። ታሪክ ወደ ኻላ ተመለሰ ማለት ነው።)
ይህን ዓላማቸውን እንዳያሳኩ እንቅፋት የሆኑት እንደነ ጀዋር ያሉ የኦሮሞ ብሄርተኞችና ህወሃት ናቸው ብለው ያምናሉ።
የኦሮሞ ብሄርተኞችን አዳክመናል ብለው ስላመኑ ህወሃት( እና ማሀበራዊ መሰረቱ የሆነው የትግራይ ህዝብ ላይ) ዘመቱ። ይሄው ነው።
3# አብይ አህመድ
ዓላማ፦
የአብይ አላማ ያልተገደበ ስልጣን፣ ዝና እና ገንዘብ ነው።
ስርዕቱ ፕረዝደንታዊ ፤ እሱም ፕረዝደንት ሆኖ እየቦረቀ ከመኖር የዘለለ ለህዝብ የሚተርፍና ለትውልድ የሚሻገር ራዕይ የለውም።
እነ ጀዋርን ያሰረውም ሆነ ይህ ጦርነት ውስጥ የገባው ለስልጣኑ ብቻ ሲል ነው።
የአብይን ጨቅላነት ኢሳያስም ርስት አስመላሾቹም ያውቃሉ። ኢሳያስ እሱን አንግሶ ሃገሪቱን ጓዳው ማድረግ የፈልጋል። ተስፋፊዎቹ ደግሞ ኦሮሞና ህወሃትን ከመታላቸው በኻላ ሊያስወግዱትና እንደነ ሙስጠፌ ባሉ የስነ-ልቦና ባሪያዎች ሊቀይሩት ያስቡ ይሆናል።
**********
እንግዲህ በዚህ አይነት ጦርነት ሰፊው ደቡብ "ምን አገኛለው" ብሎ ነው የሚገባው? ለማንስ ሲል ነው የሚማገደው? እንዲያዉም ከቻለ ነገ ከሚመጣው አስከፊ ነገር አንፃር ዛሬ መታገል ነው ያለበት። ቢያንስ ግን የማንም መጠቀሚያ መሆን የለበትም።
*****
በተረፈ ጦርነቱ አክራሪ ኢትዮጵያዊ ብሄርተኞችም(አግላዮች) ሆኑ ተስፋፊና ርስት አስመላሾቹ እንደሚመኙት አጭርና ቀላል አይሆንም።
ገና ከዉስጥ ብዙ መካካድ፣ መከፋፈልና መገዳደል የማናይበት ውስብስብ ነገር ውስጥ መግባታቸውን አላወቁም።
አምላክ ሰላማችንን ይመልስ። ለመሪዎችም የሰላም ልብ ይስጥ።
By: via Qerro Media Service - QMS
Subscribe to:
Post Comments (Atom)
Featured post
Ethiopia’s controversial quest for the sea
https://ift.tt/4t29xJd Ethiopia is famously landlocked. That’s why the ambitious Ethiopian prime minister Abiy Ahmed has long harbored visi...
-
Has your daily walk become an endless trudge to nowhere? These podcasts, chosen by comedians, podcasters, Guardian writers and readers, are ...
-
They are benevolent vegetarian gods. They watch over, through shielded eyes, the very few animals that have a fringe. William Topaz McGonag...
-
The actor’s remarkable life fed into the character of Arlette in the Netflix hit, from growing up Jewish in occupied France, via Left Bank j...
No comments:
Post a Comment