ከሌሎች የፖለቲካ ሃይሎች ፈንጠር ብለው በመቆም፣ የአብይ መንግስት ወደ ተስፋይቱ ምድር ያሸጋግረን ያሉት፣ #አብን እና #ኢዜማ ነበሩ። ኢዜማ በገዛ አዳራሹ መሰብሰብ አትችልም ሲባል ፈገግታ በታከለበት መግለጫ ሀገር እንዳይፈርስ ብዬ ትቼዋለሁ ብሏል። የተቃውሞ ሰልፍ እንዳያደርግ የተከለከለው አብንም፣ ያሻግረን ያለውን የብልጥግና መንግስት ከመቅጽበት "#አገዛዝና" "#አምባገነን" በሚሉ ስያሜዎች ወረፍ ወረፍ አድርጎ፣ ወደ ተፈቀደለት ሳሎን ተመልሷል። ነገሩ የተበላሸው፣ በ21ኛው ክፍለ ዘመን፣ ከላይ የተቀባሁ ንጉስ ነኝ የሚል ቂል፣ የኦሮሞን ወጣት እንዳሻው ሲያስደፋና ሲያስር እንዲሁም የኦሮሞ ፓርቲዎችን ለማጥፋት ሲደክም፣ አፈናው eventually ወደ እናንተ እንደሚመጣ ባለመረዳታችሁ ነው።
አዎ፣ አብይ ከልክ በላይ የነግስታቱን አሃዳዊው ዘመን ናፋቂ ነው። ለዛ ዘመን ያለው ፍቅር ቀልባችሁን እንዳሳታችሁ አሌ አይባልም። አብይ፣ ያን ዘመን የሚያንቆለጳጵሰው ግን ለአማራ ህዝብ የተለየ ጥቅም ሊሰጥ ሳይሆን፣ ብቸኛ ህልሙ፣ ተጠያቂነት የሌለበት ንግስና ስለሆነ ነው። የራሱን ህዝብና ማህበራዊ መሰረት ሙሉ ለሙሉ የከዳ ከንቱ፣ ለአማራ ህዝብ ይጠቅማል የሚል ግምት ስትወስዱ ነው ነገር የተበላሸው። አዞው መጀመሪያም ላይ አሰለፈህ፤ መጨረሻ ላይ እጣ ፈንታህ መዋጥ ነው። ይብላኝ ላንተ፣ ከኋላ ሆነህ የድጋፍ ጭብጨባ ስትሰጥ ለከረምከው።
ብልጥግና ፓርቲን የኋላ ኪሱ ውስጥ ከቶ የሚንቀሳቀሰው አብይ፣ አሁን እንኳን ተቃዋሚ ፓርቲ ሊፈራ፣ የህዝብ እንደራሴዎች የፕሮጀክት አፈፃፀም ሊጠይቁኝ ማን መብት ሰጣቸው ማለት ጀምሯል።
የአፈ ጮሌውን ተረት ተመስጠህ ስትሰማ መክረምህ ጉድ እንዳረገህ አምነህ፣ አሁን እንባህን አበስ አበስ አድርገህ ገብተህ መተኛት ነው። ከእናንተ ውስጥ የሚታሰረው ታስሮ የተረፈው በዚህ አመት ይደረጋል የተባለው ምርጫ ላይ ቢሳተፍ፣ ኢዜማም ሆነ አብን ጨዋታ ከማድመቅ ያለፈ role አይኖራችሁም። ብልጥግና ምርጫውን በዝረራ አሸንፌያለሁ ካለ በኋላ፣ ንጉሱ ከፈቀዱ አንዳንድ አመራሮች ፀባያቸው ታይቶ የመንግስታዊ ተቋማት ቦርድ ሰብሳቢነትና መሰል ሹመቶች ይወረወርላቸዋል። አሁን ዶ/ር አረጋዊ በርሄ (የህዳሴው ግድብ አስተባባሪ ኮሚቴ ሰብሳቢ) ፤ ፕ/ር በየነ ጴጥሮስ (የፖሊሲ ጥናት ኢንስቲትዩት ዲሬክተር) ፤ ፕ/ር ብርሃኑ ነጋ (የአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ቦርድ ሰብሳቢ) እንደሆኑት ማለት ነው። ባይሆን አብይን ሙሉ ለሙሉ አምነዋለሁ ያለው ፕ/ር ብርሃኑ ነጋ ምናልባት ከፍ ሊደረግለት ይችላል። ከአንድ ጉምቱ ፖለቲከኛ እንደዚህ አይነት politically naïve ንግግር መስማት ራሱ ገራሚ ነው። አሁን ባለው ሁኔታ፣ የፖለቲካ ጉዞአችሁ በዚህ መልኩ ይጠናቀቃል።
የተሻለ የሚሆነው፣ የብልጥግና ካዳሚነታችሁን ሙሉ ለሙሉ ትታችሁ መንግስት ያላግባብ ያሰራቸውን ፖለቲከኞች በአስቸኳይ ፈትቶ፣ ሁሉን አካታች የሆነ dialogue እንዲጀመር መጠየቅ ነው። ቢያንስ ለቀድሞ ወዳጆቻችሁ ለእነ ልደቱ እንኳን ጩሁ እንጂ፣ ጎበዝ። ጃዋርን ጨምሮ በእስር ላይ የሚገኙት የኦሮሞ ፖለቲከኞችም፣ ወንጀል ኖሮባቸው ሳይሆን ብልጥግናን በዝረራ እንደሚያሸንፉት ስለሚታወቅ ነው የተወገዱት። እናንተም ዝም ያላችሁት ያንን ስለምታውቁ የማሸነፍ እድላችሁ የሚጨምር ስለመሰላችሁ ነው። ሆኖም አብይ ከእናንተ ጋር ተመሳሳይ አሃዳዊ vision አለው ማለት ስልጣን ያጋራችኋል ማለት አይደለም። የህልም እንጀራ ነው።
ለማንኛውም፣ ግራም ነፈሰ ቀኝ፣ አብይ የሚባል puppeteer አልሰማ ካለ ከእነ አሻንጉሊቶቹ በህዝብ ማእበል የሚሸኝበት ቀን እንደሚመጣ ጥርጥር የለውም። የጊዜ ጉዳይ ነው። እስከዛ የሚሆነውን ማየት ነው።
~by THE FINFINNEE INTERCEPT.
By: via Qerro Media Service - QMS
Subscribe to:
Post Comments (Atom)
Featured post
Ethiopia’s controversial quest for the sea
https://ift.tt/4t29xJd Ethiopia is famously landlocked. That’s why the ambitious Ethiopian prime minister Abiy Ahmed has long harbored visi...
-
Has your daily walk become an endless trudge to nowhere? These podcasts, chosen by comedians, podcasters, Guardian writers and readers, are ...
-
They are benevolent vegetarian gods. They watch over, through shielded eyes, the very few animals that have a fringe. William Topaz McGonag...
-
The actor’s remarkable life fed into the character of Arlette in the Netflix hit, from growing up Jewish in occupied France, via Left Bank j...
No comments:
Post a Comment