አብይ አህመድና መንግሥቱ የኦሮሞ ሕዝብ ጠላት ነው፤ ሁሉም ሊታገለው የሚገባ የጭቁን ሕዝቦች ሁሉ ጠላት ነው። (Tsegaye Ararssa)
=================
አዎን፣ ሃጫሉን በግፍ የገደለው የአብይ አህመድ መንግሥት፣
ጃዋርን፣ በቀለ ገርባን፣ እና ሌሎች የኦሮሞ የፖለቲካ መሪዎችን ሁሉ በግፍ አስሮ ለሥቃይ የዳረገው የአብይ አህመድ መንግሥት፣ (አሁንም ለፖለቲካ ፍጆታ እንዲውል በማለት እነ ጃዋርን ጨምሮ ሌሎች መሪዎችንና ታዋቂ ግለሰቦችን ለመግደል የሚያሶረው ይሄ መንግሥት)፣
የኦሮሚያ ሚዲያ ኔትወርክን ዘግቶ፣ ንብረቱን ዘርፎ፣ ጋዜጠኞቹን ያለ ጥፋት አስሮ፣ የኦሮሞን ሕዝብ ያለ ድምፅ ያስቀረው የአብይ አህመድ መንግሥት፣
የኦሮሞ የፖለቲካ ፓርቲዎችን፣ በተለይም ደግሞ የኦሮሞ ነፃነት ግንባርን፣ ለማፍረስ በገንዘብ፣ በሴራ፣ እና በብረት ተደራጅቶ የተሰማራው የአብይ አህመድ መንግሥት፣
የኦሮሞን ሕዝብ ታሪክ፣ ማንነትና ባህል ለማጉደፍና ለማጠልሸት በማሰብ፣ በምንደኛ አክቲቪስቶች፣ በከሸፉ አርቲስቶች፣ ባጎደፉና ካህናትና በሆድ አደር የኑፋቄ ነቢያት፣ እንዲሁም በመንግሥትና በግል የሚዲያ ተቋማት-- በነጠላና በቡድን በሚደረግ ደቦ--ያለ ማቋረጥ፣ ለሁለት ዓመታት እየተንቀሳቀሰ ያለው የአብይ አህመድ መንግሥት፣
ኦሮሞን እየገደለው ገዳይ፣ እያጠቃው አጥቂ፣ እያጠፋው አጥፊ፣ ክልሉን እያፈረሰበት እርሱን አገር አፍራሽ በማድረግ፣ አለ ባህሉና አለ ጥፋቱ የኦሮሞን ሕዝብ--እንደ ሕዝብ--እየወነጀለ፣ ከዚህም አልፎ የሕዝቡን እውነትና ሃቅ በእራሱ ውሸትና ሸፍጥ ለመቅበር የሚጥረው የአብይ መንግሥት፣
የኦሮሚያን ክልል መሬት ለወረራ፣ የሕዝቡን ንብረት ለዘረፋ አጋልጦ፣ ገበሬውንና ልጆቹን ለችግር፣ ለስደትና ለሰቆቃ አሳልፎ ሰጥቶ፣ በሙሰኛ ባለሥልጣናቱ በኩል፣ መሬት ንብረቱን ለሽያጭ የዳረገው የአብይ አህመድ መንግሥት፣
የኦሮሚያን ክልል በ8 ክላስተሮች (clusters) ከፋፍሎ በወታደራዊ አስተዳደር ሥር (under the rule of military command posts) በማስገባት፣ ክልሉን ኢ-ሕገመንግሥታዊ በሆነ መንገድ ለማፍረስና ለባለጊዜ ነፍጠኞች አሳልፎ ሲሰጥ እጅ ከፍንጅ የተያዘው የአብይ አህመድ መንግሥት፣
የኦሮሚያን ሕገ-መንግሥት ተላልፎ (ወይም አፍርሶ)፣ የክልሉን ፕሬዚዳንት ሽሮ፣ የእራሱን ምስለኔ ሹሞ፣ መንግሥቱን አፍርሶ፣ ምርጫ አግዶ፣ ክልሉን የግል ጓሮው አድርጎ የሚያተራምሰው ወንጀለኛው የአብይ አህመድ መንግሥት፣
ክልሉን በወታደር እያሸበረ፣ ሕዝብን በብዙ አስር ሺህዎች እያሠረና እያሰቃየ፣ ትምህርት ቤቶችን (ሰሞኑን ከኢሬቻ በዓል ጋር ተያይዞ ደግሞ፣ በፊንፊኔም ጭምር) ወደ ጊዜያዊ እስር ቤት ቀይሮ፣ የምስኪን ገበሬዎችን ቤትና ሰብል በእሳት እያጋየ፣ ህፃናትንና ሴቶችን፣ ነፍሰ-ጡር እናቶችን እና ወጣት ወንዶችን ጭምር በጋጠ-ወጥ (እና ቅጥረኛ) ወታደሮቹና ካድሬዎቹ እንዲደፈሩ እያደረገ ያለው የአብይ አህመድ መንግሥት፣
በየከተማው ባደራጃቸውና ባስታጠቃቸው የሽብርና የውንብድና ቡድኖች በመታገዝ፣ የኦሮሞ ሕዝብ በራሱ ከተሞች ውስጥ ወጥቶ እንዳይገባ፣ ተንቀሳቅሶ እንዳይሠራ፣ አምርቶ እንዳይሰበስብ፣ ተቀጥሮ እንዳይሠራ፣ ነግዶ እንዳያተርፍ፣ እየገደለና እያሸማቀቀ ያለው የአብይ አህመድ መንግሥት፣
ሕገ-መንግሥታዊና ተፈጥሮአዊ የሆነውን መብቶቹን አግዶ፣ የትግል ጥያቄዎቹን አፍኖ፣ ሌላው ቀርቶ፣ ሕዝቡ፣ ባህላዊ በዓሉን--ኢሬቻን--እንኳን በአግባቡ እንዳያከብር ያደረገው የአብይ አህመድ መንግሥት፣
የእራሱ የመንግሥት ሰነዶችና መግለጫዎች ባረጋገጡት መሠረት ብቻ እንኳን፣ በ2 ዓመት ውስጥ ከ5300 ኦሮሞ በላይ የገደለውና ያስገደለው የአብይ አህመድ መንግሥት፣
በመንግሥት፣ በፓርቲና በግል በተደራጁ የፕሮፓጋንዳ ተቋማቱ በመጠቀም፣ በውሸት ትርክት ላይ በመመሥረት፣ የኦሮሞ ሕዝብ ተፈጥሮአዊ የትግል አጋር ከሆኑ ጭቁን ሕዝቦች ጋር በሰላም አብሮ እንዳይኖርና እንዳይተባበር ለማጋጨትና መሪዎቹንም ለማቃቃር ሌት ተቀን እየሠራ ያለው የአብይ አህመድ መንግሥት፣
ባጠቃላይ፣ የአገሪቱን ሕገ-መንግሥታዊ የፖለቲካ ማዕቀፍ በመናድ፣ ዴሞክራሲያዊ ምርጫን በሕገወጥ መንገድ በማገድ፣ የሕዝቦችን የዴሞክራሲ ናፍቆትና ተስፋ በማጨንገፍ፣ ግላዊ አምባገነንነትን በማንገስ፣ በከፋፋይ ትርክትና የጥቂቶችን የበላይነት በሚያጀግን ታሪካዊ ሁነቶችን መርጦ የመዘከር ሥራ (acts of selective memorializing)፣ ሕዝቦችን በማጋጨት፣ አገሪቱንና አካባቢውን የአላስፈላጊ የግጭት፣ የትርምስ ቀጣና፣ ምናልባትም የጦርነት አውድማ፣ እያደረገ ያለው የአብይ አህመድ መንግሥት
...የኦሮሞ ሕዝብ ደመኛ ጠላት ነው።
ይሄ በአብይ አህመድ የሚመራው (እና አሁን አሁን ደግሞ ለይቶለት ሕገወጥ በሆነው) የብልጥግና ፓርቲ "መንግሥት"፣ የኢትዮጵያ ጭቁን ሕዝቦች ሁሉ ደመኛ ጠላት ነው።
ይሄንን የሕዝብ ጠላት፣ ሕዝቡ--ከተቻለ ከሌሎች ጭቁን ሕዝቦች ሁሉ ጋር በትብብርና በቅንጅት፣ ካልተቻለም ለብቻው--ዛሬ፣ ተግቶ ሊታገለው፣ ነገም፣ ሊፋረደው፣ የተገባ ነው።
አዎን፣ አብይ የኦሮሞ ሕዝብ ጠላት ነው። ብልጥግናም ጸረ-ሕዝብ፣ ጸረ-ዴሞክራሲ፣ ጸረ-ሰላም ኃይል ነው።
#አብይ_ወንጀለኛ_ነው!
#ብልጥግና_መፍረስ_አመራሩም_ለፍርድ_መቅረብ_አለበት!
By: via Qerro Media Service - QMS
Subscribe to:
Post Comments (Atom)
Featured post
Ethiopia’s controversial quest for the sea
https://ift.tt/4t29xJd Ethiopia is famously landlocked. That’s why the ambitious Ethiopian prime minister Abiy Ahmed has long harbored visi...
-
Has your daily walk become an endless trudge to nowhere? These podcasts, chosen by comedians, podcasters, Guardian writers and readers, are ...
-
The actor’s remarkable life fed into the character of Arlette in the Netflix hit, from growing up Jewish in occupied France, via Left Bank j...
-
They are benevolent vegetarian gods. They watch over, through shielded eyes, the very few animals that have a fringe. William Topaz McGonag...
No comments:
Post a Comment