Qerro Media Service - QMS's Post

የጦርነቱ ተዋናዮች እና ግቦቻቸው
======================
የጦርነቱ ባለቤቶች፣ 1) አብይ አህመድና ብልጥግና፣ 2) የትምክህት ኃይሎች (የቤት የለሽ ፖለቲካ አራማጆች፣ እና የዘመኑ አዲስ ነፍጠኞች)፣ 3) ኢሳያስ አፈወርቂ ናቸው። እነዚህ ኃይሎች ጦርነቱን የሚያካሄዱበት ፍትሃዊ ግብና ዓላማ (cause) የላቸውም።

በጋራ ያላቸው ቁሳዊ ፍላጎት፣ መሬት፣ የተፈጥሮ ሃብትና ገንዘብ (በአጠቃላይ ኢኮኖሚውን) የመዝረፍ፣ የመሸቀጥ፣ እና የመቆጣጠር ጉጉት ነው።

ይሄንን ቁሳዊ ፍላጎት ለማሟላት፣ ሶስቱም ወገኖች፣ አብይን፣ በጉልበትም ሆነ በሸፍጥ፣ በሴራም ሆነ በቅጥፈት፣ በሥልጣን ላይ ማቆየት የግድ ሆኖ ይታያቸዋል። ይሄንንም ለማድረግ ሲሉ፣ በትብብር ጦርነት ያካሄዳሉ። (የስግብግቦች የዘረፋና የንጥቂያ ጦርነት [A robbers' war of brigandage, a war of plunder and looting]!)።

አሁን እየተካሄደ ያለው ጦርነት፣ ኢኮኖሚውን ለመቆጣጠር ከሚሻ ስብግብግብነት ባሻገር፣ ሌላ ዓላማና ግብ የለውም። (ለነገሩ ዘራፊና ሌባ፣ ከዚህ ሌላ ዓላማ ከየት ያመጣል?) ከዚህም የተነሳ፣ ጦርነቱ ፍትሃዊ ግብና ዓላማ (just cause) የሌለው ሆኗል።

ከቁሳዊ መሻት ባሻገር፣ ሶስቱንም የጦርነቱን ተዋናዮች በአጋርነት የሚያያይዛቸው ስሜት (sentiment)፣ ለጭቁን የኢትዮጵያ ሕዝቦች (በተለይም ለ"ሌሎቹ" የኢትዮጵያ ሕዝቦች) ያላቸው፦
ሀ) ምክንያት-የለሽ ጥላቻና ፍርሃት (phobia)፣
ለ) ትምክህት፥ እብሪትና ጀብደኝነት፣ እና
ሐ) ቂምን የመበቀል ፍላጎት ነው።

ከዚህ የተነሳ፣ ሶስቱም፦
1) ዴሞክራሲን (ምርጫን)፣
2) ሕብረ-ብሔራዊነትን፣ እና ፌደራሊዝምን፣
3) የሕዝቦችን በራስ የመተዳደር መብትን አምርረው ይቃወማሉ፣ ለማጥፋትም ይፋለማሉ።

ምክንያታቸውስ?

1) ዴሞክራሲና ምርጫ ከተካሄደ (በቅርቡ በትግራይ እንደተደረገው)፣ ያለ ገደብ በሥልጣን መቆየትም ሆነ በዘፈቀደ ሥልጣንን መጠቀም አይቻልም። በዴሞክራሲ መኖር ምክንያት፣ በሕግና በሕዝብ ይሁኝታ ያልተገደበ ሥልጣን ከሌለ ደግሞ፣ ቁሳዊ የመሬት፣ የሃብትና የገንዘብ ዘረፋን ማካሄድ አይቻልም። ለዚህ ነው ሶስቱም በኢትዮጵያ ውስጥ ምርጫ እንዳይኖር በጽኑ የታገሉትና ምርጫውን ያስቀሩት። ለዚህም ነው ትግራይ ላይ በትብብር ጦር ያዘመቱት። ዴሞክራሲ ካለ፣ ዘራፊና ቀማኛ የሰፈር ጉልቤ እንደልቡ መሆን አይችልምና።

2) የፌደራል ሥርዓት ካለና ክልሎች እራሳቸውን ካስተዳደሩ፣ ስልጣን በአንድ ቡድን ወይም ግለሰብ እጅ ተማክሎ ለግል ጥቅም መዋል አይችልም። እራሱን በማስተዳደር መብቱ ተጠቅሞ አንድ ክልል ምርጫ ማድረጉ፣ የተማከለ አምባገነናዊነትን ለመተግበር ስለማይፈቅድ፣ በእነዚህ ጸረ-ዲሞክራሲ አድመኞች ይጠላል፣ ይወጋል። እራሱን በራሱ ከሚያስተዳድር ክልል፣ መሬትን፣ የተፈጥሮ ሃብትንና፣ ገንዘብን መዝረፍ የሚቻል ስለማይሆን፣ እንደዚህ ዓይነት ክልል፣ ደመኛ ጠላታቸው ይሆናል። እነሱም፣ በጸረ-ዴሞክራሲያዊነታቸው ላይ የጸረ-ፌደራሊስት ቁመናን ይጎናጸፋሉ።

የብሔሮች ሉዓላዊነትና የራስን ዕድል በራስ የመወሰን መብት፣ የብሔሮችን ሰብዓዊ ክብር (fundamental human dignity)፣ የወል አድራጊነት (collective agency)፣ እና የራስን ፍጻሜና ግብ (one's own destiny) መወሰን መብት ከተከበረ፣ ብሔሮች የአገር ባለቤት ስለሚሆኑ፣ እነዚህ ዘራፊዎች እንደልብ እየገቡ፣ ዘረፋቸውን መፈጸም አይችሉም። በዚህም ምክንያት፣ የሕዝቦችን ሉዓላዊነት፣ ማንነትና ህልውና ይቃወማሉ። ለማጥፋትም ይታገላሉ። በጸረ-ዴሞክራሲያዊነትና በጸረ-ፌደራሊስትነታቸው ላይ፣ ጸረ-ሕዝብነትን (ጸረ-እኩልነትን) ይደርባሉ።

በመሆኑም፣ እነዚህ የጦርነቱ ሶስት ተዋናዮች--ማለትም፣ የአብይ አምባገነናዊ ቡድንና ብልጥግና፣ የትምክህትና የነፍጠኛ ሥርዓት አቀንቃኞች (ማለትም፣ ትናንትንና ርስትን አስመላሽ ነን ባዮች)፣ እና አምባገነኑ ኢሳያስ--በዴሞክራሲ፣ በፌደራሊዝምና በብሔሮች ሉዓላዊነት መብት ላይ ውጊያ ለመፈጸም በማሰብ፣ በአንድነትና በትብብር፣ የመጨረሻውን ጦርነት በትግራይ ላይ ባወጁት ጦርነት እየከወኑት ይገኛሉ።

በዴሞክራሲ፣ በፌደራሊዝም፣ እና በህዝቦች ሉዓላዊነት ላይ የተቃጣው ይሄ ጦርነት፣ በትግራይ ላይ ብቻ የተቃጣ ሳይሆን፣ በሁሉም የኢትዮጵያ (ሌሎች) ሕዝቦች ላይ የተቃጣ ጥቃት ስለሆነ፣ ሁሉም ብሔሮች በጽናት ሊመክቱት ይገባል፤ እየመከቱትም ይገኛሉ። ድሉም የነሱ ነው።

#ስግብግባችሁንና_ከሃዲያችሁን_እዛው_ቤተመንግሥት_ፈልጉ_ለማለት_ነው።
#Survive_outfight_outlive_outlast_Abiy's_war!



https://youtu.be/MaUAJkjoKBg
By: via Qerro Media Service - QMS

No comments:

Post a Comment

Featured post

Ethiopia’s controversial quest for the sea

https://ift.tt/4t29xJd Ethiopia is famously landlocked. That’s why the ambitious Ethiopian prime minister Abiy Ahmed has long harbored visi...